The 1st Breast Cancer Awareness Walk in ETHIOPIA!!
የጥቅምት ወር የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ አለምፀሀይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን (ኤቢሲኤፍ) ከቀድሞ የሊሴ ገ/ማርያም ተማሪዎች ጋር እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን የተዘጋጀው የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ የ 5 ኪ.ሜ የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡ በእለቱም ወ/ሮ ሂወት ሰለሞን ጤና ሚኒስቴርን ወክለው ድጋፋቸውንና የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በውጭ እና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ለመርዳት የተቋቋመው አለምፀሀይ የጡት ካንሰር ፋውንዴሽን (ኤቢሲኤፍ) ራሱን የቻለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን የጡት ካንሰር ምርመራ እና ህክምና የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እና የገንዘብ አቅም ለሌላቸውን ሴቶች ድጋፍ ያደርጋል፡፡