ከአሜሪካ የመጡ እና የኢትዮጵያ ኗሪ የሆኑ ቤተሰቦች አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን በመጎብኘት ድጋፍ አደረጉ

ከአሜሪካ የመጡ እና የኢትዮጵያ ኗሪ የሆኑ ቤተሰቦች አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን በመጎብኘት ድጋፍ አደረጉ፡፡

አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን በጎንደር እና በአዲስ አበባ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ በጡት እና በማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እና በሌሎችም የካንሰር ታማሚዎች እና አሰታማሚዎችን የመጠሊያ ፤የምግብ ፤የግል ንፅህና መጠበቂያ ፤የትራንስፖርት አገልግሎት ከተለያዩ የሃገሪቷ ክፍል የሚመጡ እና በጥቁር አንበሳ አስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተካተሉ ለሚገኙ ወገኖቻችን አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኝ ማእከል ነው ፡፡

ጎብኚዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት በማእከሉ የሚገኙ እናቶች እህቶች እና አስታማሚዎች የሚደረግላቸው ድጋፍ በመልከታቸው የማእከሉን መስራችና የማእከሉን ሰራተኞች አመስግነው ለዚ የበጎ ፈቃድ ስራ እኛም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን ብለዋል፡፡

በቀጣይም የበጎ ፈቃድ ድጋፍ አባል ለመሆን እና የበኩላችውን ድርሻ ለመወጣት ቃል በመግባት ጉብኝቱ ተጠናቋል፡፡

የበጎ ፈቃድ የድጋፍ አባል ለመሆን በዚ አደራሻ የደውሉ +251942418558 ወይም +25194060406 USA 678229615

ቅድመ ምርመራ እና የካንሰር ግንዛቤ ህይዎትን ያድናል

Early detection and awareness of cancer saves lives!

cancerawarness #pinkhouse www.abcfonline.org

ABCF pinkhouse

AlemFre PinkHouse Cancer Foundation (APCF) is a nonprofit organization dedicated to helping Ethiopian women abroad and at home, who are burdened with financial need to access screening, diagnosis, and treatment for breast cancer. APCF is also devoted to guiding Ethiopian women to optimal health through increased awareness about breast, Cervical, and other cancer and diseases associated with cancer.

https://www.abcfonline.org
Previous
Previous

ዶክተር አለማየሁ በቀለ እና ቤተሰቦቻቸው ለአለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን የስድስት መቶ ሺ ብር(600.0000)፣ መድሃኒት እና የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

Next
Next

Pink House Visitors የሆስፒስ ኢትዮዽያ አባላት አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽንን ጎበኙ