Pink House Visitors የሆስፒስ ኢትዮዽያ አባላት አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽንን ጎበኙ
ከሆስፒስ ኢትዮዽያ የመጡ እግዶች የአለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽንን የስራ እንቅስቃሴ ለማየት በማእከሉ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል የማእከሉ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አቶ እስክንድር ላቀው ለጎብኚዎቹ ሲያስረዱ ማእከሉ በጎንደር እና በአዲስ አበባ ስራውን እየሰራ እደሚገኝና በቀጣይ በባህርዳር ፤በጂማ ፤በሃረር ቢሮ ለመክፈት በጥናት ለይ እደሆነ አስረድተው አለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን በአራት አመት ውስጥ በጎንደር እና በአዲስ አበባ ለሰባት ሺ አምስት መቶ በላይ የጡት እና የማህፀን ጫፍ የካንሰር ታማሚዎችን ከአስታማሚዎች ጋር የመጠሊያ የምግብ የግል ንፅህና መጠበቂያ የትራንስፖርት አገልግሎት ድጋፍ እያደረገ እደሚገኝ አስረድተዋል
ከሆስፒስ ኢትዮዽያ የመጡት ዶክተር ኤፍሬም በበኩላቸው( በፓሌቲቭ ኬር) ህመምን እዳይሰማ በማድረግ ዙርያ ከማእከሉ ጋር አብረው እደሚሰሩ ተናግረው በቀጣይ ማእከሉን በተለያዩ የቅድመ ምርመራ መሳሪያዎቸ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
www.abcfonline.org
cancerawarness #pinkhouse www.abcfonline.org
ድጋፍ ለማድረግ: ንግድ ባንክ 1000464499591
በቴሌ ብር መተግበሪያ
አቢሲኒያ ባንክ፡ 18294001
ቡና ባንክ፡4489527000284