አለማቀፍ አመታዊ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ወር
አለማቀፍ አመታዊ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ወር ምክኒያት በማድረግ በጎንደር ቅርንጫፋችን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኦንኮሎጂ ክፍል ጋር በመተባበር ግንዛቤ በመስጠት አሳልፈናል። ቀን 24/05/16
ሰላም ጤና ይስጥልን እንዴት አላችሁ
አለምፍሬ ፒንክ ሀውስ ካንሰር ፋውንዴሽን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ኦንኮሎጅ ክፍል በጋራ በመሆን የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ ወርን አስመልክቶ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴት ሰራተኞች በሙሉ እና ጥሪ ለተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን አሳልፈናል።
ዶ/ር መኳንንት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ክሊኒካል ዳይሬክተር፣ የካንሰር ክፍል ዶክተሮች ዶ/ር እዩኤል፣ዶ/ር አማረ የሽጥላ፣ዶ/ር ኤፍሬም እና ከፓቶሎጅ ክፍል ዶ/ር ጥሩ ዘር በተገኙበት ስለ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥተዋል፣ በመቀጠል በድርጅታችን/ ፒንክ ሀውስ/ የተሰሩ ስራወችን እና በቀጣይ አገልግሎቱን በሰፊው ለመስጠት ፣የሰውን ህይወት ለመታደግ የሁሉም ማህበረሰብ ርብርብ እንደሚያስፈልግ በዝርዝር አቅርበናል።
በመጨረሻም ዶ/ር መኳንንት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር እንዳሉት በዓለማችን ብሎም በሀገራችን እየተስፋፋ የመጣውን በሽታ ለመቀነስ እና ለማጥፋት፣ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ከጎናችን ሆኖ እየሰራ ለሚገኘው አለምፍሬ ፒንክ ሀውስ ካንሰር ፋውንዴሽን ምስጋናቸውን አቅርበው ከተቻለ በገንዘብ ፣በዓይነት፣ በሙያዊ ድጋፍ ፒንክ ሀውስን ሁሉም ሰራተኛ በተቻለው አቅም መደገፍ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።