አለም ፍሬ ፒንከ ሃውስ ካንሰር ፋውዴስን ሳምታዊ ትምህርታዊ ፕሮግራም አከናወነ
አለምፍሬ ፒንከ ሃውስ ካንሰር ፋውዴስን በማእከሉ እየተረዱ ህክምናቸውን ለሚከታተሉ ታካሚዎች እና አስታማሚዎች በየሳምቱ ከየካ ጤና ጣቢያጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት አየሰጠ ይገኛል በዛሬው እለት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር እና የተለያዩ እንግዶች፤ የማእከሉ ባለሙያዎች በተገኙበት በግል እና በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ዙርያ ተጓዳኝ በሽታዎችን መከላከልን አስመልክቶ ትምህርት ከሰጡ በኋላ የጤና ጣቢያ ባለሙያው በማእከሉ ለሚገኙ ታካሚዎች በጤና ጣቢያው ደረጃ የሚሰጡ ማንኛውንም ህክምና በማእከሉ በመገኘት እደሚሰጡ ገልፀዋል የአለምፍሬ ፒንክሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን አምባሳደር አቶ እስክንድር ላቀው ለታካሚዎች በጥንካሬ በብረታት ህክምናቸውን በመጨረስ ወደ መጡበት መመለስ እዳለባቸው አሳስበው የእለቱ ትምህርት ተጠናቋል የአለም ፍሬ ፒንክ ሃውስ ካንሰር ፋውዴሽን ከክልል መተው ለሚታከሙ ማረፊያና ምግብ በማቅረብ ይታወቃል።
ቅድመ ምርመራ እና የካንሰር ግንዛቤ ህይዎትን ያድናል
Early detection and awareness of cancer saves lives!
#pinkhouse www.abcfonline.org