ቅዳሜ ጥር 18 2016 አዲስ አበባ ፒንክሀውስ
ሰላም እንዴት አላችሁ የአለምፍሬ ፒንክሀውስ ካንሰር ፋውንዴሽን ቤተሰቦች እንደተለመደው ሳምንታዊ የጤና ውይይታችንን ከየካ ጤና ጣቢያ በመጡ ባለሙያዎች እና አዳዲስ በመጡ የታካሚዎቻች ጥያቄ ቀኑን አሳልፈናል፣ እንዲሁም ወ/ሮ ባንቺአምላክ (Cancer Survivor) ካንሰርን ያሸነፈች በፒንክሀውስ ለታካሚዎቻችን ልምዷን ለማካፈል በመካከላችን ተግኝታለች፣ ካንሰርን ማሸነፍ እንችላለን፣ ሀኪም የሚያዝልን የህክምና መድሀኒቶች እና ክትትሎችን በአግባቡ ከተገበርን እና ተስፋ ካልቆረጥን ድል ማድረግ እንችላለን በማለት ገልፃልናለች። የካ ጤና ጣቢያ በየሳምንቱ ለምታደርጉልን የባለሙያ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናችኋልን፣ ወ/ሮ ባንቺአምላክ በፒንክሀውስ በመገኝት ልምድሽን ስላካፈልሽ እናመሰግንሻለን።
ቅድመ ምርመራ እና የካንሰር ግንዛቤ ህይዎትን ያድናል
Early detection and awareness of cancer saves lives!
#pinkhouse www.abcfonline.org
Facebook (https://www.facebook.com/apcfpinkhouse)
Twitter(X) (https://twitter.com/APCFPinkHouse)
Instagram (https://www.instagram.com/abcpinkhouse?igshid=ZDdkNTZiNTM%3D)