ቅዳሜ ታህሳስ 13 2016 አዲስ አበባ ፒንክሀውስ
ቅዳሜ ታህሳስ 13 2016 አዲስ አበባ ፒንክሀውስ
በፒንክሀውስ ነባር ታካሚዎች ቆይታቸውን/አገልግሎታቸውን ጨርሰው ሲውጡ በተመሳሳይ በየሳምንቱ የተለያዩ በአቅምም በገንዘብም ደከም ያሉ አዳዲስ ታካሚዎች አገልግሎቱን ለማግኝት ቦታውን ይተካሉ፣ እኛም በየሳምንቱ ለሚመጡ አዳዲስ ታካሚዎች መደገም ያለበትን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች እና በአዳዲስ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤዎችን እንሰጣለን፣ጥያቄዎችንም እንዲጠይቁ እናደርጋለን።
በዚህኛው ቅዳሜም የድርጅታችን የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አቶ እስክንድር ላቀው ፣ የድርጅታችን የስራ ሀላፊዎች እና እንግዶች በተገኙበት እንደተለመደው ከየካ ክ/ከተማ በመጡ አዳዲስ እና ነባር ባለሙያዎች በአካባቢ ንፅህና አጠባበቅ፣ተጓዳኝ በሽታውችን እንዴት መከላከል እንደሚችሉ እና በታካሚዎች በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ጥሩ ቅዳሜን አሳልፈናል፣እንደሁልጊዜው ታካሚዎቻችን በየካ ጤና ጣቢያ ደረጃ መሰጠት ያለባቸውን ነፃ አገልግሎቶች እና መድሀኒቶችን እንደሚያገኙ እና ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው ባለሙያዎች ገልፀውልናል።የድርጅታችን አምባሳደር የሆኑት አቶ እስክንድር ታካሚዎች በጥንካሬ እና በብርታት ህክምናቸውን ጨርሰው ወደ ቀደመው ህይዎታቸው መመለስ እንዳለባቸው አስገንዝበው ሳምንታዊ የቅዳሜ ውይይታችን በዚህ መልኩ አጠናቀናል።
ቅድመ ምርመራ እና የካንሰር ግንዛቤ ህይዎትን ያድናል'
Early detection and awareness of cancer saves lives!
cancerawarness #pinkhouse www.abcfonline.org
ድጋፍ ለማድረግ: ንግድ ባንክ 1000464499591
በቴሌ ብር መተግበሪያ
አቢሲኒያ ባንክ፡ 18294001
ቡና ባንክ፡4489527000284