ቅዳሜ 8 2016 አዲስ አበባ ፒንክሀውስ
እንደሁልጊዜው በቅዳሜ የጤና ውይይታችን እንግዶች እና የጤና ባለሙያዎች ተገኝተውበታል።
በአብዛኛው ከአገራችን የገጠሩ ክፍል የሚመጡ የካንሰር ታማሚዎች እንደሚሆኑ ይነገራል የተለያዩ ምክኒያቶች ቢኖሩትም፣ በጊዜ ወደ ጤና ተቋም አለመሄድ፣ ካንሰር የሚተላለፍ በሽታ አድርጎ መቁጠር እና አስታማሚ ከጎን ማጣት፣ የተለያዩ ጭሶችን መታጠን /ወይራ ጭስ እና የመሳሰሉት/ በጊዜ ሂደት ለካንሰር እንደሚያጋልጥ እና ያለ አቻ ጋብቻ ለማህፀን ካንሰር እንደሚዳርግ ግንዛቤ ሰጥተናል።
የካ ክ/ከተማ ጤና ጣቢያ እያደረጋችሁት ላለው ድጋፍ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
የድርጅቱ መስራች ዶር ፍሬሂዎት በመካከላችን በመሆን ግንዛቤ ስጥተውናል፣ የጤና መኮነን ሀጎስ እና ሲስተር ሰላም ከየካ ጤና ጣቢያ፣ ዶር ህሊና /wings of healing/ ስለመጣችሁ እና ግንዛቤ ስለሰጣችሁን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።
'ቅድመ ምርመራ እና የካንሰር ግንዛቤ ህይዎትን ያድናል'
Early detection and awareness of cancer saves lives!